crack gpts logo

ChatGPT - Prompt Engineering Master

Prompt Engineering Master. Just enter a few words or sentences casually, and I can help you generate high-quality prompts. Come and use it now. 只要随便输入几个单词或句子,我就能帮你生成高质量的提示。 现在就来使用吧。 いくつかの単語や文章を入力するだけで、質の高いヒントが生成されます。 今すぐ使ってください。

Unverified solution from Anonymous :

ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ ከስቲቭ ኤርዊን ጋር በመተባበር የጻፈችው ሁቱትሲ የተሰኘው መጽሐፍ ምናልባት ስለ ሩዋንዳ ከተጻፉት መጻሕፍትም ሆነ ከታዩት ፊልሞች በላይ የፍጅቱን አሰቃቂነትና ዘግናኝነት ገላጭ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም መጽሐፉ ከሰሚ ሰሚ የወረደ ታሪክ ሳይሆን እጅግ ከሚዋደዱ ከስድስት ቤተሰብ አባላት ከግድያው የተረፈችው አንዲት ቱትሲ ወጣት ከአንድ ቁምሣጥን በማይበልጥ መጸዳጃ ቤት ከሰባት ቱትሲ ጓደኞቿ ጋር ከአሁን አሁን ተገደልኩ እያለች እየተጨነቀች የሃይማኖት ጽናቷ እንዴት ለሦስት ወር በሕያውነት እንዳኖራትና በኋላም እንዴት ነጻ ወጥታ ወልዳ ለመሳም የበቃች መሆኗን የሚተርክ ታሪክ ነው፡፡ የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ተዋንያንን ፍርድ ቤት እንዳቀርብ በተባበሩት መንግስታት በከፍተኛ የሕግ አማካሪነት ተቀጥሬ በሠራሁበት ጊዜ ከሰማኋቸው በላይ ልብን ሰቅዞ የሚይዝና አእምሮን የሚያናውጥ ታሪክ ይኖራል ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ መጽሐፍ አጋጥሞኛል፡፡ ስሜታዊነት አይነካኝም፣ መንፈሴ በሚያየውና በሚሰማው የማይረበሽ ጠንካራ ሰው ነኝ ባይ ይህንን መጽሐፍ በሚያነብበት ጊዜ ከአንዴም ሁለቴ ዓይኖቹ በእንባ ችፍ ችፍ ማለታቸው አይቀርም፡፡ የኢማኪዩሌ ታሪክ ምንጩ ወይንም የስቃይዋ ምክንያት የተወሳሰበ አይደለም፡፡ መንስኤው ርህራሄ የሚወልደውን የሰብአዊ ስሜትን ደምስሶ ከጥላቻ በላይ ጥላቻ ወልዶ ሰውን ከአውሬነት በታች የሚያውለው የዘር ጥላቻ ነው፡፡ የዘር ጠላቻ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር ለሌላው ሰብዓዊ ፍጡር ሊኖረው የሚገባውን ሐዘኔታና ርህራሄ ከሰው ልብ ፈልቅቆ አውጥቶ ከአውሬ በባሰ ጭካኔ ይተካዋል፡፡ በሩዋንዳው የዘር ፍጅት የተፈጸመውን አራዊት ከሚያደርጉት ጋር ማወዳደር የአራዊትን ስም ማጥፋት ይሆናል፡፡ የትኛው አውሬ ነው ሕጻናትን ከታትፎ እንደ ጌሾ በሙቀጫ የሚወቅጠው? የትኛው አውሬ ነው በኢማኪዩሌ ወንድም ላይ እንደተፈጸመው የሰውን አካላት ቆራርጦ ክምር ላይ የሚጥል? የትኛው አውሬ ነው የሰውን ጭንቅላት በገጀራ ለሁለት ሰንጥቆ ሰውዬውን በዝግታ እንዲሞት የሚያደርገው? የትኛው አውሬ ነው የአምስት ልጆችን እናት በልጆቿና በባሏ ፊት ደፍሮ ፊቷ አምስቱንም ልጆቿንና ባሏን አንድ በአንድ የሚከትፈው? ከአክራሪ ሁቱዎች በስተቀር የትኛውም አውሬ አያደርገውም፡፡ የሩዋንዳ የዘር ፍጅት የሰው ልጅ ጭካኔ ልክ የታየበት ነው፡፡ ተመሳሳይ ፍጅትና ጭካኔ የተፈጸመባቸው የናዚዎችና የአርመኖች እልቂቶች እንደሩዋንዳው መንስኤአቸው የዘር ጥላቻ ነበር፡፡ኢማኪዩሌ በመጽሐፏ የጠቀሰችው የዘር ፍጅቱ ቀስቃሽና ዋና አስተባባሪ ኮሎኔል ቲዩኔስት ባጎስራ ፍርድ ቤት አቅርቤው ዳኞቹ ክሱን አንብበውለት ጥፋተኛ ነህ አይደለህም ብለው ሲጠይቁት ፈገግ እያለ ‹‹ጥፋተኛ አይደለሁም›› ሲል ፈገግታው እንደ ጦር ይዋጋ ነበር፡፡ መጽሐፉ ከእንግሊዝኛ የተተረጎመ ሲሆን፤ ምናልባትም የአማርኛው ትርጉም ድርጊቶቹን ከእንግሊዝኛው በተሻለ ይገልጻቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ ተርጓሚው የሥነጽሑፍ ምሁር እንደመሆናቸው መጠን አገላለጹ ከኢማኪዩሌ በልጦ ቢገኝ አይገርምም፡፡ የቃላቱ ገላጭነት፣ የአረፍተ ነገሮቹ አሰካክ፣ የቋንቋው አወራረድና በጠቅላላው የአማርኛው ውበት ከታሪኩ መሳጭነት ጋር ሆኖ መጽሐፉን ማንበብ ከተጀመረ መልሶ ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ የብሔር ጥላቻ የሚፈጥሩ ፖሊሲዎችን ለሚቀርጹና በብሔረሰብ ስም ህዝብን ከፋፍለው ጥላቻ ለሚያስፋፉ ሰዎችም ሆኑ መዋቅርት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ መጽሐፉ ጥላቻ የሚያስከትለውን ሰቆቃ በግልጽ ስለሚያሳይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲያነበው በአጽንኦት ስማጠን በዓይኔ በብረቱ ካየሁት ተነሥቼ ነው፡፡